ትምህርት 1
ብሉይ ኪዳንን ለምን እናጠናለን?
ሀ. መግቢያ
ለብዙ ሰዎች ብሉይ ኪዳን በምስጢር የተንቆጠቆጠና የተሞላ ነው። በአብዛኛው እንደተለመደው አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነብ ሲነገረው ከአዲስ ኪዳን እንዲጀምር ይነገረዋል፤ አለፍም ካለ መዝሙረ ዳዊትን ያነብባል። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ህትመቶች አዲስ ኪዳንንና መዝሙረ ዳዊትን ብቻ ይዘው ይታተማሉ።
ብዙ ክርስቲያኖች ለረዥም ዘመን አዲስ ኪዳንን ብቻ ያነብቡና ብሉይን ሊያነብቡ ጎራ ሲሉ መረዳት ስለሚያቅታቸው ጥቂት የኦሪት መጽሐፍትን ከማንበብ በቀር እልፍም ማለት ያቅታቸዋል። ያን ጊዜ ተመልሰው ወደ አዲስ ኪዳናቸው ይመለሳሉ።
የዚህ ችግር መንስኤው ብሉይ ኪዳን የተረዱ ጥቂቶች መሆናቸውና በብሉይን በአዲስ ኪዳን መካከል ያለው ግንኙነት ስለማይታያቸው ነው። ማንኛውንም መደበኛ መጽሐፍ ለማንበብ ስንጀምር ከመሃል አይደለም። እንደዚያ ሲሆን የመጽሐፉ ሙሉ ታሪክን መረዳት አንችልም ማለት ነው። በአለም ላይ ልዩ የሚባለውን መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስንም ስናነብብ ልንረዳ የሚገባን 66 መጽሐፍት በውስጡ ያሉት፥በ40 ጸሃፊዎች የተጻፈ፤2000 አመት በላይ ያስመዘገበ አንድ ወጥ መጽሐፍ መሆኑን ልንረዳ ይገባል።
ለ. ብሉይ ኪዳንን ለምን እናጠናለን?
- በመጀመሪያ ብሉይ ኪዳን የቅዱሳት መጽሐፍት አንድ አንበሳውን ድርሻ የሚይዝ፤ ለትምህርትና ለተግሳዕ የተጻፈ ክፍል ነው። (2ጢሞ.3፡14~17)
- የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት በውስጣቸው መለኮታዊ ጥበብን ተላብሰዋል
- የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት የድነትን መንገድ ያመላክታሉ
- የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት መለኮታዊ ምሪትን እናገኝባቸዋለን።
- የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ጥሪያችን የተሳካ እንዲሆን መለኮታዊ ትጥቅን ያስታጥቁናል።
- 1ጴጥ.1፡12~13 እንደሚነግረን
- ብሉይ ኪዳን ለትምህርታችን ተጽፎልናል
- ብሉይ ኪዳን የተጻፈው በብሉይ ዘመን ለነበሩት ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን እድሜ ውስጥ ላለነው ለኛ ለትምህርት እንዲሆን ተብሎ ነው።
- የብሉይ መጽሐፍት በአዲስ ኪዳን ዘመን ለእ/ር ክብር ተቀድሰን እንድንኖር የሚረዱን ቅዱሳት መጽሐፍት ናቸው።
- 1ቆሮ.10፡6፤11 ስናነብ የሚከተሉትን ሁለት ቁም ነገሮች እናገኛለን፡
- ብሉይ የጻድቃንን አሉታዊና አዎንታዊ ታሪክ ያለሽፍንፍን እንድንማርበት ለትምህርታችን ግልጽ አድርጎ ያስቀምጥልናል።
- ብሉይ ኪዳን የተጻፈው በተለይ በመጨረሻው ዘመን ላለነው ክርስቲያኖች በመከራና በፈተና ጸንተን እንድንቆም የሚመክር እውነትን ያስተምራል።
- ዕብ.10፡1 እንደሚነግረን ብሉይ ኪዳን የአዲስ ኪዳን ጥላ ነው። ጥላው ሁልጊዜ የሚያመለክተው ገሃድና እውን የሆነውን አዲስ ኪዳንን ወይን አካሉን የሚጠቁም ነው። (ቆላ.2፡16~17፤ ዕብ.8፡5)
- ብሉይ ኪዳን የማይታየውን እውነት በምሳሌያዊ መንገድ አድርጎ በገሃድ ያቀርባል
- ለምሳሌ፦
- ብሉይ ኪዳን ፍጥረታዊ ሲሆን አዲስ ኪዳን መንፈሳዊ ነው
- ብ.ኪ. በስጋ የሚደረግ አዲስ ኪዳን ግን በመንፈስ የሚደረግ ነው።
- ብ.ኪ ጥላ አዲስ ኪዳን አካል ነው
- ብ.ኪ. በእጅ የተሰራ አ.ኪ በእጅ ያልተሰራ መቅደስ ያለው ነው
- ብ.ኪ. ምሳሌያዊ አ.ኪ ሰማያዊ ነው
- ብ.ኪ.ጊዜያዊ አዲስ ዘላለማዊ ነው
- ብ.ኪ በማየት አዲስ ኪዳን በእምነት የሚኖርበት ህይወት ነው
- እንደተመለከትነው የብሉይ ኪዳን ትምህርት ፍጥረታዊ ሆኖ ለመንፈሳዊው መንገድ ጠራጊ ነበር (1ቆሮ.15፡44~47)
- ፍጥረታዊ ውልደት የመንፈሳዊ ውልደትን ምሳሌ ነው። (ዮሃ.3፡5)
- ፍጥረታዊ እስራኤል የመንፈሳዊ እስራኤልን ምሳሌ ናት (ገላ.6፡16)
- ፍጥረታዊ ኢየሩሳሌም መንፈሳዊቱን ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ታመለክታለች (ዕብ.12፡22)
- ምድራዊ መቅደስ የሚመጣውን መንፈሳዊ መቅደስን ያመለክታል (1ጴጥ.2፡5)
- ፍጥረዊ ክህነት መንፈሳዊዉን ክህነት ይጠቁማል (ዕብ.13፡16)
- ፍጥረታዊ ጠላቶች እና ጦርነቶች ለመንፈሳዊ ውግያና ጦርነት ምሳሌዎች ናቸው (ኤፌ.6፡12)
- ሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳችን ብሉይ ኪዳንንም ጨምሮ የቤዛችን የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ነው። (ማቴ. 5:17; ሉቃ. 24:27, 44; ዮሃ. 1:45; 5:39, 46-47; ሐዋ. 10:43; ገላ. 3:24; ዕብ. 10:7).
- ሉቃ.24፡25~27
- መጽሐፍ ቅዱሳችን በአንድ ላይ የሚናገረው ብዙ ቅንጥብጣቢ ታሪኮችን ሳይሆን ወጥ የሆነው የእግዚአብሔር የሰውን ዘር በክርስቶስ የማዳን እቅድን ነው።
- የመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱሳችን ሁለት ምዕራፎች እና የመጨረሻዎቹ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ መደምደሚያ የሆነው የዮሃንስ ራዕይ መዝጊያ ምዕራፎች የሃጢአትን መጀመሪያንና መደምደሚያን ያበስራሉ። በመካከል ያሉት ምዕራፎች ሁሉ የሚያወሩት በክርስቶስ ስለመዋጀት ነው። ስለዚህ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳችንን የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ መጽሐፍ ብንለው አንሳሳትም።
- ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን የተመሰረተበት የመሰረት ድንጋይ ነው። (ዕብ.3፡1፤ ኤፌ.2፡20)
ክፍል 2
1 ብሉይ ኪዳንን ማን ጻፈው?
ብሉይ ኪዳን ብለን የምንጠራው ከፍጥረት እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ድረስ ያለውን ታሪክ የሚተርከውን ክፍል ሲሆን በውስጡ 39 መጽሐፍትን ይዟል። ቅዱሳን መጻሕፍት የተጻፉት ከ1,600 ዓመታት በሚበልጥ ጊዜ ውስጥ በኖሩ 40 የሚያህሉ ሰዎች ነው። የሚገርመው ነገር ግን እነዚያ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መልእክት ምንጭ እንደሆኑ አልተናገሩም። ከጸሐፊዎቹ አንዱ "የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ" በማለት በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፉ ተናግሯል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16)
(2 ሳሙኤል 23:2 እንደሚነግረን "የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ" ብሏል። ከዚህ ለመመልከት እንደምንችለው ጸሐፊዎቹ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መልእክት ምንጭ የአጽናፈ ዓለሙ የበላይ ገዥ የሆነው አምላክ እንደሆነ እንደተናገሩ ጥርጥር የለውም።
- የመጀመሪያዎቹ 5 የኦሪት መጽሐፍት በሙሴ እንደተጻፉ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ተናግረዋል። (ዘጸዓት. 17:14፤ 34:27፤ ኢያሱ. 8:31፤ ዳንኤል. 9:13፤ ሉቃስ 24:27፣ 44) ።
- ከዚያም ኢያሱ፣ ሳሙኤል፣ ዳዊት፣ እና ሌሎችም ተከታዮቹን መጽሐፍት በአምላክ መንፈስ ተመርተው ጻፉ። እንደ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ህዝቅኤል የመሳሰሉትም ነቢያት የትንቢት መጽሐፍቱን ጽፈዋል።
- ከመጀመሪያዎቹ 39 መጻሕፍት መካከል አብዛኞቹ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፉ ሲሆን የተወሰኑት ክፍሎች ደግሞ በአረማይክ ቋንቋ ትእነዚህ ተጽፈዋል። እነዚህ 39 ቅዱሳት መጽሐፍ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ወይም “ብሉይ ኪዳን” በመባል ይታወቃሉ።
- በሶስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ብሉይ ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክኛ 70 የሚሆኑ የአይሁድ ሽማግሌዎች ተረጎሙት። ይህም ትርጉም በእንግሊዘኛ Septuagint በግዕዝ ደግሞ ትስዓቱ ቅዱሳን የተረጎሙት በመባል ይታወቃል።
- ብሉይ ኪዳንን ስናስብ ሌላው ዋና ነገር ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ቢኖር የተጻፈበት ህብረተሰብ ይኖርበት የነበረውን የአኗኗርና ባህል ነው። ብሉይ ኪዳንን አንድ ዘመናዊ ሰው በራሱ ዘመን ባህልና ማህበረሳዊ ግንዛቤ ካነበበው የቅዱሳት መጽሐፍትን ትርጉም የሚያዛባ ይሆናል። ሆኖም ግን ብሉይ ኪዳን የተጻፈበትን ቀደምት ባህልና አኗኗር መረዳት መልዕክቱ በሚገባ ለመረዳት ይረዳል። ብሉይ ኪዳን የተጻፈው በመካከለኛው ምስራቅ ባህልና ቋንቋ ነው። ለምሳሌ፡ የብሉይን ጋብቻ ታሪክ ስናነብ የመካከለኛው ምስራቅ ጋብቻ ስርዓት እንደሆነ ልንረዳ ይገባናል።
የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት አከፋፈል
ብሉይ ኪዳን አራት መሠረታዊ ክፍፍሎች አሉት፦
- የሕግ መጻሕፍት ፦ እነዚህ መጻሕፍት የሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መሠረት የሆኑት አምስቱ የሙሴ መጻሕፍትናቸው። የእስራኤል ሕዝብ አጀማመር ታሪክንና የሕይወትና የአምልኮን መመሪያ የያዙ ናቸው። እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡
- ኦሪት ዘፍጥረት
- ኦሪት ዘጸአት
- ኦሪት ዘሌላውያን
- ኦሪት ዘኊልቊ
- ኦሪት ዘዳግም
- የታሪክ መጻሕፍት ፦ በነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የእስራኤል ሕዝብ በተስፋዪቱ ምድር ውስጥ ያሳለፉትን ታሪክይተርካሉ። በዚህም ውስጥ እንዴት የተስፋዪቱን ምድር እንደያዙ፣ ራሱን የቻለ መንግሥት መመሥረታቸው፣ ወደስደት በምርኮ መሄዳቸውና ስኬታማው የመቃብአውያን አብዮትን ያካትታሉ።
- መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ
- መጽሐፈ መሳፍንት
- መጽሐፈ ሩት
- መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
- መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
- መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
- መጽሐፍ ነገሥት ካልዕ
- መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
- መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
- መጽሐፈ ዕዝራ
- መጽሐፈ ነህምያ
- መጽሐፈ አስቴር
- መጽሐፈ ኢዮብ
- የጥበብ መጻሕፍት ፦ ይኼኛው ጎራ ላይ የተካተቱት መጻሕፍት በሥነ ፍጥረት ላይ ልዩ እይታንና ጽብረቃንየሚያደርጉና በቤተሰባዊ ሕይወትና በአስተዳደራዊ ሂደት ሞራላዊ ማለትም ግብረ ገባዊ የአናኗር መመሪያዎችን፣መልካም የሆኑ መስተጋብሮችንና ፈሪኀ እግዚአብሔርን የሚመለከቱ ጽሑፎችን ይዘዋል።
- መጽሐፈ ኢዮብ
- መዝሙረ ዳዊት
- መጽሐፈ ምሳሌ
- መጽሐፈ መክብብ
- መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
- የትንቢት መጻሕፍት ፦ ደግሞ በክፉዎች ላይ ፍርድን፤ ለተጨቆኑት ደግሞ የተስፋ መጽናናትን የሚሰጥየእግዚአብሔር ቃል ይገኝባቸዋል።
- ትንቢተ ኢሳይያስ
- ትንቢተ ኤርምያስ
- ሰቆቃወ ኤርምያስ
- ትንቢተ ሕዝቅኤል
- ትንቢተ ዳንኤል
- ትንቢተ ሆሴዕ
- ትንቢተ አሞጽ
- ትንቢተ ሚክያስ
- ትንቢተ ኢዩኤል
- ትንቢተ አብድዩ
- ትንቢተ ዮናስ
- ትንቢተ ናሆም
- ትንቢተ ዕንባቆም
- ትንቢተ ሶፎንያስ
- ትንቢተ ሐጌ
- ትንቢተ ዘካርያስ
- ትንቢተ ሚልክያስ
ብሉይ ኪዳንን እንዴት እናጥና?
- በታሪካዊ ቅደም ተከተል Chronologically
- ምን ታሪክ ከምን ታሪክ ቀጥሎ ተጻፈ ብለን ታሪካዊ ቅደም ተከተሉን ይዘን ማጥናት አንደኛው የማጥኚያ መንገድ ነው።
- ኪዳናዊ ቅደም ተከተል Covenantally
- በዚህ ኣጠናን በብሉይ ኪዳን የተሰጡትን 9 ኪዳናት ተራ በተራ ከአዲስ ኪዳን ጋር በማገናዘብ ማጥናት ሁሉኑም የብሉይ ኪዳን በዝርዝር እንድናጠና ይረዳናል።
- መሲሃዊ አጠናን Messianically
- ይህ አጠናን ደግሞ በብሉይ ኪዳን የመሲሁ ጥላ የሆኑትን ነገሮች በማየትና መሲሃዊ ትንቢቶችን በመመርመር የሚደርግ ጥናት ነው። በአጭር ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስን እያገላበጡ መፈለግ ማለት ነው።
መግቢያSed ut perspiciatis unde omnis iste natus error sit voluptatem accusant doloremque laudantium, totam rem.
|
Skill TwoSed ut perspiciatis unde omnis iste natus error sit voluptatem accusant doloremque laudantium, totam rem.
|
Skill ThreeSed ut perspiciatis unde omnis iste natus error sit voluptatem accusant doloremque laudantium, totam rem.
|