ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ አለማችን ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዘች ያለች ትመስላለች። አንዳንዶች አዲስ የአለም ስርዓት (New World Order) እንደተመጀረ አድርገው ሲመለከቱ ሌሎች ደግሞ የሰው ዘር ከቁጥጥር ውጪ ወጥቶ ወደ መዳረሻው አስጊና ወደማይታወቅ ታላቅ ውዥንብር ውስጥ እየገባ መሆኑን ይናገራሉ። እንደ ጥንት ዘመን በማለዳ የእለቱን ዜና አንብቦ መውጣት አስደሳች ዜና መሆኑ ቀርቷል። ቀን በቀን ጆሮን የሚሰቀጥጥና የአለም ችግር እየጨመረና ከግምት በላይ እየሆነ መጥቷል። ታዲያ ምን ቀጥሎስ ምን ሊመጣ ነው? የሚለው ጥያቄ በሰው ዘር ሁሉ ውስጥ የሚያቃጭል ሆኗል።
ከፊት የሚመጣው ዘመን በትንቢት መነጽር አይተው የሚነግሩን እነማን ይሆኑ? በየዘመኑም ሊመጣ ያለውን እናውቃለን የሚሉ “መሳይ ነቢያት” ነበሩ። እንደነ ኖስትራዳሙስ፣የፋቲማ ልጆች ወዘተ. የሚባሉ ተነስተው በአለም የሚመጣው እንዲህና እንዲህ ነው ብለው የመሰላቸውን ተናግረው አልፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰው ዘርና ስለምንኖርባት አለም መጨረሻ ምልክቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። ስለወደፊቱ ለማወቅ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በአስተማማኝ ሁኔታ ጥያቄውን ሊመልስለት ወደሚችለው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መምጣት አለበት! ታሪክ የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛነት በተደጋጋሚ በተፈጸሙት ትንቢቶች አመልክቷል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተፈጸሙና ያልተፈጸሙ ትንቢቶች አሉ። የተፈጸሙት አሁን ላለንበት ብዙ ባያሳስቡንም፤ ሊፈጸሙ ያሉት ግን እጅግ ሊያሳስቡን ይገባል። ከ2000 አመታት በፊት ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን እንዲህ ብለው ጠየቁት “ንገረን…. የመምጣትህና የአለም ፍጻሜ መቼ ይሆናል?” ለዚህ ጥያቄያቸው የሰጣቸው መልስ የዘመኑ ፍጻሜ ሲሆን የሚያውቁበትን ምልክቶችን ነበር። ተቃዋሚ የኀይማኖት ምሁራን ኢየሱስን ሲቃወሙ “ከሰማይ ምልክት” እንዲያሳያቸው ለተናገሩት ምላሽ ሲሰጣቸው ጌታ እንዲህ አለ፦ “1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።2 እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በመሸ ጊዜ። ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ፤3 ማለዳም። ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ትቶአቸውም ሄደ።” በዚህ ዘመን ስለአየር ጠባይ ሁኔታ የሩቅና የቅርቡን አይተው የሚተነብዩ ዘመናዊ መሳሪያዎች ያሉበት ዘመን ነው፤ነገር ግን ያለንበትን ዘመን ምልክቶች ለመረዳት አይኖቹን እንደጨፈነ ሰው ሆነናል። በዚህም ከቀደሙ ዘመናት ፈሪሳውያን በብዙም አልተለየንም ማለት ነው። የዚህ ዘመን ትውልድ ግን የትንቢት መደምደሚያ የደረሰበት ትውልድ እንደሆነ ሊረዳ ይገባል። |
1. ሰባቱ ዘመናት (The Seven dispensations)
2. የናቡከደነጾር ህልም (The dream of Nebuchadnezzar) 3. ጦርነት (War) 4. ረኀብ (Famine) 5. ቸነፈር (Pestilence) 6. የመሬት መንቀጥቀጥ (Earthquake) 7. ወንጀልና ግፍ (Crime & Violence) 8. የሰይጣን አምልኮ (Occult) 9. ጸረ ክርስቶስ (Antichrist) 10. 666 (The Number of the Beast) 11. የመከራው ዘመን (Tribulation Period) 12. የእውቀት መብዛት (Increase of Knowledge) 13. ፍርድ (Judgement) 14. የሺህ ዓመት መንግስት (Millennium Reign of Christ) 15. የወንጌል መስፋት (Spread of the Gospel) 16. ንጥቀትና አርማጌዶን (Rapture & Armageddon) 17. ትንቢተ ዳንኤል (Book of Daniel) 18. መጓጓዣና አደጋዎች (Speed & Accident) |
|